የArab Health ኤግዚቢሽን ከተለያዩ ሀገሮች የሚመጡ በጤና አገልግሎትና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ የተሰማሩ አምራች፣ ምርት አከፋፋይና አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያዎችን እና የመንግስት ተቋማትን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ በየዓመቱ የሚካሄድ ትልቅ ኹነት ሲሆን፣ የዘንድሮው እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ 30 እስከ ፌብሪዋሪ 02 ቀን 2013 ዓ.ም በዱባይ ዓለምአቀፍ ንግድ ማዕከል (DWTC) እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኤግዚቢሽኑ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትርና የዱባይ ገዥ Sheikh Mohammed bin Rashid Al Maktoum አልጋ ወራሽ Sheikh Hamdan bin የተከፈተ ሲሆን፣ ከሰባ የተለያዩ ሀገራት የተሳተፉ ከሦስት ሺህ በላይ ኤግዚቢተሮች ምርታቸውንና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ ተገኝተዋል፡፡
 
በትናትናው የኤግዚቢሽኙ ወሎ ቆንስላ ጽ/ቤታችን በDubai Health care city (DHCC) በኩል የተመቻቸለትን መድረክ በመጠቀም የሀገራችንን የጤናና ፋርማሲዩቲካል ሴክተር ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድሎቻችን ተሳታፊ ኩበንያዎች የማስተዋወቅ ሥራ ተሰርቷል፡፡ በመድረኩ ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ የመስኩን አማራጭ የኢንቨስትመንት ዕድሎቻችን በገለጻ ያቀረቡ ሲሆን፣ የውጭ ኩባንያዎች እንዲሰማሩባቸው መንግስት የቅዲሚያ ትኩረት ከሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች የስፔሻሊቲ ጤና አገልግሎት እና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ የመጀመሪያዎቹ መሆናቸውን በማንሳት፣ በመስኩ ለሚሰማሩ ኢንቨስተሮች ስለሚሰጡ ማበረታቻዎችና የመንግስት ድጋፍ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 
በመጨረሻም ፍላጎት አሳይተው ለሚመጡ ኩባንያዎች በቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተገናኝተው መነጋጋር እንዲችሉ እና ተጨባጭ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን መጎብኘት እንዲችሉ ቀጠሮ የማመቻቻትና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች የሚሰጥ መሆኑም ተገልጾላቸዋል።

Disclaimer: The official text of the website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram