በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በሰዓሊ ብሩክ የሽጥላ የተዘጋጁ ስዕሎች የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በቆንስላው ቅጥር ግቢ ውስጥ ተካሂዷል። በዝግጅቱም ላይ የተለያዩ የዐረብ ኤምሬት ዜጎች፣ አፈሪካውያን እንዲሁም አምባሳደሮች፣ በተ.ዐ.ኤም የሚኖሩ የተያየ ዜግነት ያላቸው የጥበብ አፍቃሪያንም ታድመዋል።
በዝግጅቱ ላይ ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ስሆን በንግግራቸውም ኢትዮጵያ በጥበቡ ዘርፍ ላይ ከጥንት ጀምሮ ትልቅ አሰዋፅኦ ማድረጓን፣ በዓለም አቀፍ ደረጇ የሚታወቁ የስዕል ጥበቦች እንዳሏት ገልጸው ከዚህም በመነሳት በጥበቡ ዓለም ስሟን ክፍ ያደረጉ አርቲስቶች ማፍራቷን ገልፀው አርቲስት ብሩክ የሽጥላም በስዕሉ አለም ትልቅ አስተዋጽዖ እያበረከተ የሚገኝ የዘመናችን ሰዓሊ መሆኑን፣ ብዙዎቻችን አይቻልም የምንለውን እንደሚቻል በማሳየቱ ለብዙዎች ምሳሌ በመሆኑ ክብር ይገባዋል ሲሉ ጠቅሰዋል።
ከአውደ ርዕይዩ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ስነ-ስርዓት እንዲሁም ባህላዊ ምግቦቻችን የዕራት ግብዣ የተካሄደ ሲሆን አምባሳደር አክሊሉ የቡና ታሪካዊ አመጣጥን ታሪክ አንስተው ለታዳሚዎቹ ስለቡና አመጣጥ ታሪክና በዚህም እረገድ ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ሀገር መገኛ መሆኗን አስረድተዋል።
በአርቲስቱ የተዘጋጁት ስዕሎች በታዳሚው የተጎበኙ ሲሆን ከፍ ያለ አድናቆትም አስገኝቶለታል።
AmharicArabicEnglish

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram