በቆንስላ ጽ/ቤት ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማዘመን በተገቢው ጥራትና ፍጥነት ለመፈጸም የሚያስችል የአሰራር ስርዓት (Automation System) ለመዘርጋት ስምምነት ተደረገ፤
 
በቆንስላ ጽ/ቤት በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል እና ዘመኑ የሚፈልገውን የአሰራር ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ ዜጎች አገልግሎቶችን ለማግኘት በሚፈልጉበት ወቅት ጊዜና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ አገልግሎት ለመስጠትና የመረጃ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችል የCustome Relationship Management System ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ለማድረግና የአሠራር ስርአቱን ለመዘርጋት በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር በጨረታ ከተመረጠው የTATATECH Technology Products and Education ከተባለው ድርጅት መካከል የውል ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል።
በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ፣ የኮሚኒቲ የቦርድ አመራሮችና አባላት የተገኙ ሲሆን ዘመናዊ የአሰራር ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ልናገለግለው የቆምለትን ዜጋ ተሳቢ ያደረገና የምንኖርበትንም ሀገር የሚገኙ ልምድና ተሞክሮዎችን በመቀመር ዜጎች የትኛውንም አገልግሎት ሳይቸገሩ ባጭር ጊዜና በጥራት እንዲያገኙ ማድረግና መረጃም በሚፈለግበት ወቅት በቀላሉ ማግኘት፣ ፈጣን ውሳኔ መስጠት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት በአጭር ጊዜያት ውስጥ ተግባራዊ ማድረግን ታሳቢን ያደረግ እንደሆነ ተጠቅሷል።
AmharicArabicEnglish

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram