የዱበይ ኢንቨስትመንቶች ፓርክ በስሩ ሰባ (70) የሚደርሱ ትልልቅ ኩባንያዎች ያቀፈ ሲሆን፣ ከኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት በሀገራችን ትልቅ የኢንቨስትመንት ፓርክ በመገንባት ለኢንዱስሪዎች ማምራቻ፣ በከፍተኛ ደረጃ የትምህርትና ጤና አገልግሎት ለሚያቀርቡ ተቋማትና የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በማልማት ከዋና ከተማችን አዲስ አበባ ብዙም ሩቅ ባልሆነ አካባቢ የኢንዱስትሪ መንደር እውን እንዲሆን ከፓርኩ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች መካሄዳቸው ይታወሳል፡፡
 
በተመሳሳይ ሁኔታ የፓርኩ ልዑካን ቡድን የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት በማካሄድ ውሰኔ ላይ ለመድረስ እንዲያግዘው በበየነ መረብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመገናኘት በዝርዝር ጉዳዮች ላይ የቴክኒክ ውይይት ለማድረግ ፍላጎት በመቅረቡ፣ ዛሬ እ.ኤ.አ ጁላይ 28/2022 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተወካዮች በተገኙበት ስኬታማ የበየነ መረብ ውይይት ተካሄዷል፡፡
 
በውይይቱ መጨረሻ ለውሳኔ የሚያግዙ የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ፍቃድ ሰነዲ ቅጂ፣ የመንግስት-የግል ሽርክና ኢንቨስትመንት (Joint Venture) ኮንትራት ናሙና እና በፓርኩ ውስጥ በግል የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትና ማከፋፈል የሚያስችል ፍቃድ የተመለከተ ሕግ ቅጂ በመለዋወጥ ወደ ውሰኔ ለመድረስ የሚያስችል ዕድል መኖሩ ታውቋል፡፡
AmharicArabicEnglish

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram