በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት እና በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያውያን እና የትውልደ ኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር በጋራ በመተባበር የ2015 ዓ.ም አዲስ ዓመት ዋዜማ፣ የአንድነት ቀን እና የኮሚኒቲ ማህበር የዩቱብ ሬዲዮ ምረቃ ልዩ የበዓል ዝግጅት ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ.ም በዱባይ ከተማ ተከበረ፡፡
 
በዝግጅቱ ላይ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ የልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ተወካዮች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ተሳትፈዋል።
በበዓሉ ላይ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስል ጄኔራል ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ በክብር እንግድነት በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዚሁ መሰረት ሀገራችን ባለፈው የ2014 ዓ.ም ብዙ ፈተናዎችና ተግዳሮቶች ተጋርጦባት እንደነበር አስታውሰው ፣ የውጭና የውስጥ ኃይሎች ተጣምረው የሀገራችንን ሉዓላዊነት በመፈታተን ግልጽ ጥቃት መክፈታቸውን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም የአሸባሪውን የሕወኃት ቡድን ወረራ ለመመከት ኢትዮጵያውያን በአንድነት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ተጋድሎ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
 
በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙት የሀገራችን ጠላቶች በግንባር ከሚደረገው ጦርነት ባልተናነሰ ሁኔታ የማህበራዊ ግንኙነት ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሀገራችን ላይ የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት የሀገራችንን ስም በማጉደፍ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሀገራችን ጉዳይ የተሳሳተና የተዛባ መረጃ እንዲኖር በማድረግ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል። ይህን ሀሰተኛ መረጃና ውሸት ለመከላከል ትክክለኛና የሀገራችንን ነባራዊ እውነታ የተመለከቱ መረጃዎችን ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
በ2014 ዓ.ም የታየው የሕዝባችን አንድነት እና ሕብረት ሀገራችን በጠንካራ መሰረት ላይ እንድትገኝ ማድረጉን ስናብር ስናምር የሚለው መሪ ቃል የሀገራችንን ባህል፣ ታሪክ የኛነታችንን ጥንካሬ እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በተለይ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከአልባሌ ከፋፋይ ጉዳዮች ርቀው በአንድነት ፣በሕብረትና በመተሳሰብ አዲሱን 2015 ዓ.ም እንድንቀበል ጥሪ አቅርበዋል።
በአዲሱ 2015 ዓ.ም በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ለህብረተሰቡ የተቀላጠፋ አገልግሎት ለመስጠጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል። ከዚህም አንጻር በዛሬው ዕለት በይፋ ስራውን የሚጀምረው የኮሚኒቲ የዩቱብ ሬዲዮ ፕሮግራም ዋነኛ ሲሆን ዜጎች ወቅታዊ መረጃ እንዲኖራቸውና እርስ በርስ የማስተዋወቅ ስራዎች በቀጣይ እንደሚሰራ ተገልጿል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ከቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ እና ከኮሚኒቲ ማህበሩ ጋር ተቀራርቦ እንዲሰራና ተሳትፎ እንዲያደርግ አምባሳደር አክሊሉ ከበደ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን አዲሱ ዓመት የሰላም እና የደስታ እንዲሆን ተመኝተዋል።
 
ፕሮግራሙ ላይ በሀገራችን በችግር ላይ ለወደቁና ለተፈናቀሉ ዜጎቻችን ድጋፍ እንዲሆን ከኅብረተሰቡ ድጋፍ የሚሰባሰብበት የቃል መግቢያ ሰነድ ተሰጥቶ ድጋፍ እንዲሰባሰብ ተደርጓል።
በተጨማሪም በበዓሉ ላይ የተለያዩ አዝናኝ የባህል ማስተዋውቂያ ፕሮግራሞች በዱባይ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕጻናትና ወጣቶች የቀረበ ሲሆን ፕሮግራሙ በሁሉም የሃይማኖት አባቶች ጸሎት እንዲከፈት ተደርጓል።
 
AmharicArabicEnglish

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram