“የሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላብሮቭ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት ውጤታማ ነበር”
ክቡር አምባሳደር መለስ ዓለም
(ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ/ም አዲስ አበባ):የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ክቡር አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ፣አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
ክቡር አምባሳደር መለስ ዓለም በማብራሪያቸው እንደ ገለጹት የሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያያ ደረጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ውጤታማ ነበር ብለዋል ።
ቃል አቀባዩ በማብራሪያቸው ክቡር ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መወያዬታቸውን ገልጸዋል።
ቃል አቀባይ ክቡር አምባሳደር መለስ ዓለም ክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ባደረጉት ዉይይት ኢትዮጵያ እና ሩስያ አሁን ላይ ያላቸዉን መልካም የሚባል የፖለቲካ ግንኙነት በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በግብርና እና በኃይል እና ኢነርጂ አማራጮች ማስፋት እንደሚገባቸው ገልጸዋል ነው ያሉት።
ክብርት ፕሬዚደንቷ የባለብዙ ወገን ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስርዓት መፈተሽ እና መታደስም አለበት፤ሩስያ የአፍሪካን የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባልነት እንደምትደግፍ መግለፃቸውን ቃል አቀባዩ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል ።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ እና ሩስያ ግንኙነትታሪካዊ፣ በሁኔታዎች የማይቀየር እና ዘመናትን የተሻገረ መሆኑን አንስተዋል ያሉት አምባሳደር መለስ፥
ከቀድሞዋ ሶቭት ህብረት ዘመን ሲነከባለል የቆየ ቀሪ ብደር፤ብደር ለልማት(Debt for Development) ወደ ሚል ፓኬጅ በመለወጥ የኢትዮጵያ መንግስትን የልማት ጥረት ለመደገፍ ሩስያ ወስናለች።
በዚህም የመልካዋከና የኃይል ማመንጫን ለማዘመን፣የባልቻ ሆስፒታልን የቴክኒክ አቅሙን ለማሳደግ(የህክምና መሳሪያዎችን ለመግዛት እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማሟላት) እንዲውል መወሰኑንም ጠቅሰዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤት አገራችን በተደጋጋሚ አጀንዳ ሆና በቀረበችበት ወቅት፣ ተገቢ ያልሆኑ ተፅዕኖዎችን በመከላከል ከሩሲያ ፌዴሬሽን በመርህ ላይ የተመሰረተ ድጋፍ በመደረጉ ክቡር አቶ ደመቀ ምስጋና መቸራቸውን አምባሳደር መለስ ገልጸዋል።
ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የሕዳሴውን ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ኢትዮጵያ በመርህ ተመስርቶ ፍሬያማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ያላትን አቋም መግለጻቸውንም ቃል አቀባዩ ጨምረው አብራርተዋል።
ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በበኩላቸው ቀደም ሲል የተቋቋመው የሁለቱ ሀገራት የጋራ ኮሚሽን ዝርዝር ስራዎችን እንዲያከናውን፡- በድርድር ላይ ያሉ ስምምነቶች እንዲጠናቀቁ፣ የተፈረሙት እንዲፀድቁ እና የፀደቁት ደግሞ ወደ ትግበራ እንዲገቡ ተስማምተዋል።
ቀጣዩን ጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በሚቀጥለዉ ዓመት እንዲደረግ መስማማታቸውን እንደገለጹ አምባሳደር መለስ በመግለጫቸው አንስተዋል።
ሚኒስትር ላቭሮቭ የሀገራት ሉዓላዊነት በእኩል ደረጃ እንዲከበር ሩስያ እንደምትሰራም ማረጋገጣቸውንም አስታውሰዋል።
በሌላ በኩል ክቡር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ በህገወጥ መንገድ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ሀገራት ዜጎችን ህጋዊ የማድረግ ምዘገባን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ እስካሁን ድረስ 58,833 የዉጭ ሀገራት ዜጎች መመዝገባቸውን ይፋ አድርገዋል ።
ቃልአቀባዩ ተመዝጋቢዎቹ ከካናዳ ፣አሜሪካ ተመዝጋቢዎቹ ከካናዳ ፣አሜሪካ ፣ኮንጎ፣ ናይጄሪያ፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ሱዳን፣ ደቡብሱዳን፣ ቻይና፣ ኤርትራ፣ ከቡርንዲ፣ ጋና፣ ባንግላዲሽ፣ሕንድ፣ላይቤሪያ፣ካሜሮን እና ጣሊያን የመጡ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ ምዝገባ እስከ ሐምሌ25 ቀን 2014ዓ/ም በመሆኑ የሚመለከታቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች እንዲመዘገቡ አሳስበዋል።
AmharicArabicEnglish

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram