የዜጎች ክትትልና ድጋፍ ማስጠበቅ
- ማንነትን የሚገልጽ አሮጌ ወይም አዲስ ፓስፖርት/ ፓስፖርትኮፒ/ ኤምሬት አይዲ መታወቂያ/ የኮሚኒቲ አባልነት መታወቂያ፤ የቪዛ ኮፒ፣ የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒዎች ወዘተ፣
- አመልካች የሚያመለክተውን ጉዳይ በጽሁፍ በማዘጋጀት በአካል ማቅረብ ይኖርበታል፣
- ቅሬታ የሚያቀርብበት አካል / ድርጅት/ ወይም ግለሰብ/ ኤጀንሲ/ ተድቢር መረጃ የስልክ አድራሻ፣ መካኒ ቁጥር ወዘተ፣
- የአመልካች ሙሉ አድራሻ/ ስልክ ቁጥር/ የሚሰራበት መ/ቤት አድራሻ ወዘተ፣
- ከአሰሪ ጋር የሚኖር የደመወዝ ጥያቄዎች ውልና ስምምነት የተፈራረሙበት መረጃ፣ አሰሪ ቤት እያሉ ደመወዛቸውን ወደ አገር የላኩበት ደረሰኝ ኮፒ፣ ወይም ደመወዝ ሲቀበሉ የፈረሙት ዶክመንት፣
- ከአገር ቤት ለስራ ያስመጣቸው ግለሰብ/ ኤጀንሲ/ ተድቢር ስምና አድራሻ፤ የቪዛ ኮፒ፣
- ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ውጭ የሰሩበት አገር መታወቂያ ወይም ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- በፍርድ ቤት የተያዙ ጉዳዮች በተመለከተ የፍርድ ቤት ሂደት ዶክመንቶች፣ የኬዝ ቁጥር፣ ኬዙ የተከፈተበት ፖሊስ ጣቢያ ስምና አድራሻ ስልክ ቁጥር ወዘተ፣
- ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ ዜጎች በተመለከተ ህክምና የወሰዱበት ሆስፒታል ስም፣ የህክምና ማስረጃዎች፣ ሪፖርቶች ወዘተ፣
- ማረሚያ ቤት ያለ ዜጎች በተመለከተ የማረሚያ ቤቱ ስም የተከሰሱበት ኬዝ ቁጥር፣ የተከሰሱበት ምክንያት፣ የታራሚ ቁጥር፣ ፓስፖርት ቁጥር ወዘተ፣
- የሟች ዜጎች ጉዳይ ለመከታተል የሟችን ማንነት የሚገልጽ ሰነድ፣ ፓስፖርት፣ መታወቂያ አይዲ፣ የሟች አሰሪ ወይም ካምፓኒ ስልክ ቁጥርና አድራሻ የኆሽፒጻል መረጃ ወዘተ፣