Shipping Human Remains

የዜጎች ክትትልና ድጋፍ ማስጠበቅ

  • ማንነትን የሚገልጽ አሮጌ ወይም አዲስ ፓስፖርት/ ፓስፖርትኮፒ/ ኤምሬት አይዲ መታወቂያ/ የኮሚኒቲ አባልነት መታወቂያ፤ የቪዛ ኮፒ፣ የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒዎች ወዘተ፣
  • አመልካች የሚያመለክተውን ጉዳይ በጽሁፍ በማዘጋጀት በአካል ማቅረብ ይኖርበታል፣
  • ቅሬታ የሚያቀርብበት አካል / ድርጅት/ ወይም ግለሰብ/ ኤጀንሲ/ ተድቢር መረጃ የስልክ አድራሻ፣ መካኒ ቁጥር ወዘተ፣
  • የአመልካች ሙሉ አድራሻ/ ስልክ ቁጥር/ የሚሰራበት መ/ቤት አድራሻ ወዘተ፣
  • ከአሰሪ ጋር የሚኖር የደመወዝ ጥያቄዎች ውልና ስምምነት የተፈራረሙበት መረጃ፣ አሰሪ ቤት እያሉ ደመወዛቸውን ወደ አገር የላኩበት ደረሰኝ ኮፒ፣ ወይም ደመወዝ ሲቀበሉ የፈረሙት ዶክመንት፣
  • ከአገር ቤት ለስራ ያስመጣቸው ግለሰብ/ ኤጀንሲ/ ተድቢር ስምና አድራሻ፤ የቪዛ ኮፒ፣
  • ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ውጭ የሰሩበት አገር መታወቂያ ወይም ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  • በፍርድ ቤት የተያዙ ጉዳዮች በተመለከተ የፍርድ ቤት ሂደት ዶክመንቶች፣ የኬዝ ቁጥር፣ ኬዙ የተከፈተበት ፖሊስ ጣቢያ ስምና አድራሻ ስልክ ቁጥር ወዘተ፣
  • ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ ዜጎች በተመለከተ ህክምና የወሰዱበት ሆስፒታል ስም፣ የህክምና ማስረጃዎች፣ ሪፖርቶች ወዘተ፣
  • ማረሚያ ቤት ያለ ዜጎች በተመለከተ የማረሚያ ቤቱ ስም የተከሰሱበት ኬዝ ቁጥር፣ የተከሰሱበት ምክንያት፣ የታራሚ ቁጥር፣ ፓስፖርት ቁጥር ወዘተ፣
  • የሟች ዜጎች ጉዳይ ለመከታተል የሟችን ማንነት የሚገልጽ ሰነድ፣ ፓስፖርት፣ መታወቂያ አይዲ፣ የሟች አሰሪ ወይም ካምፓኒ ስልክ ቁጥርና አድራሻ የኆሽፒጻል መረጃ ወዘተ፣

 

Disclaimer: The official text of the website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram