ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ ከዱባይ ኢንቨስትመንት ፓርክ ኮርፖሬሽን ምክትል ሊቀመንበርና ዋና ስራ አስኪያጅ ክቡር Mr. Khalid Jassim Mohamed Bin Kalban ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎችና ፍላጎት ዙሪያ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት የዱባይ ኢንቨስትመንት ፓርክ ኮርፖሬሽን በተመሳሳይ ስታንዳርድ በሀገራችን የኢንዱስትሪ ፓርክ ለማልማት ፍላጎት ማሳየቱን በመግለጽ፣ በቀጣይ ቀጠሮ በመገናኘት የቴክኒክ ውይይት እንደሚደረግ ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሰረት ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ ዛሬ እ.ኤ.አ ጁላይ 14/2022 ዓ.ም የዱባይ ኢንቨስትመንት ፓርክ ጄኔራል ማኔጄር Mr. Omar Al Mesmar እና የዓለም አቀፍ ንግድ ማኔጄር Mr. Salim Al Hajeri በመቀበል የቴክኒክ ውይይት ተካሄዷል፡፡ በውይይቱም ስለሀገራችን መልከም ገጽታና አማራጭ የኢንቨስትመት ዕድሎች ቪዲዮ ለዕይታ የቀረበ ሲሆን፣ የግል የውጭ ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ መሰማራት እንደሚችሉ፣ በሂደቱም ስለሚጠበቅባቸው ቅድመ ዝግጅት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ስለሚሰጣቸው ድጋፍና ማበረታቻዎች፣ እንዲሁም ስለኢንቨስትመንት ዋስትና ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ የፓርኩ የስራ ኃላፊዎች የተዘገጀላቸው መሬት የሚገኝበት አድራሻና ስፋቱ ምን ያህል እንደሆነ፣ ለሚገነበው የኢንቨስትመንት ፓርክ የሚውል ኃይል በግል ስለመምራት እና ሌሎች ዝርዝር ቴክኒካዊ ምላሽ የሚጠይቁ ሀሳቦችን አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በግብርና ኢንቨስትመንት የመሰማራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑም ተነስቷል፡፡
በመጨረሻም የኮርፖሬሽኑ ልዑካን ቡድን በሀገራችን የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት ከማድረጉ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የሚሳተፉበት የበየነ መረብ ውይይት በማዘጋጀት ዝርዝርና ጥልቅ ውይይት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለማካሄድ ስምምነት ተደርጎ የእለቱ ስብሰባ ተጠናቋል፡፡

Disclaimer: The official text of the website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram