መቀመጫውን አሜሪካ ካደረገ European Digital University እና በዱባይ ከሚገኝ የBlockChain Technology Center በጋራ በመሆን የBlock Chain Technologyን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ቴክኖሎጂውን በስፋት ማስተዋወቅና ማስተማር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከቆንስላ ጄኔራላችን ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
የBlock Chain Technology በዘመናችን በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኝ ቴክኖሎጂ ሲሆን በተለይም በፋይናንሺያል ሴክተሩ ውስጥ የጎላ ሚና እየያዘ መምጣቱን በመግለጽ ቴክኖሎጂው የወደፊቷን ዓለማችነን የሚቆጣጠር በመሆኑ ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ የሚፈልግ መሆኑን በመግለጽ ድርጅቶቹ አፍሪካ በቴክኖሎጂው ተጠቃሚ መሆን እንድትችል በቅርቡ በናይሮቢ ሴሚናር በማዘጋጀት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ ኢትዮጵያም ተሳታፊ እንድትሆን ጋብዟል።
ቆንስል ጄኔራሉ በበኩላቸውም ከድርጅቱ የተሰጠውን ገለጻ በማዳመጥ በሀገራችን በኩል በተለይም በፋይናንሺያል ሴክተሩ ያለውን ፖሊሲ በማብራራት በቀጣይ አብሮ መሥራት የሚቻልባቸው ዕድሎች ሲፈጠሩ በጋራ ለመሥራት እንደሚቻል ገለጻ ተሰጥቷል፡፡

Disclaimer: The official text of the website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram