በዱባይ የፊሊፒንስ ሪፐብሊክ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የሥራ ጉብኝት ተካሄደ።
 
በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስል ጄኔራል ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ዱባይ በሚገኘው የፊሊፒንስ ሪፐብሊክ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የሥራ ጉብኝት በማድረግ ከፊሊፒንስ ሪፐብሊክ ቆንስል ጄኔራል H.E. Marford M.Angeles ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም በሁለቱ ሀገራት ከዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት እና የዜጎችን መብት እና ጥቅም ማስከበር ጋር ተያይዞ እየተከናወኑ ባሉ ሥራዎች ዙሪያ ልምድ ልውውጥ ማድረግ ተችሏል።
ጉብኝቱም ቆንስላ ጽ/ቤታችን እያከናወናቸው ያሉ የማሻሻያና የማዘመን ሥራዎች እንዲሁም በሀገር ደረጃ በዘርፉ እየተደረጉ ለሚገኙ የለውጥ ሥራዎች የሚጠቅሙ ግብዓቶች የተገኙበት ሆኗል።
ፊሊፒንስ በውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት መልካም ተሞክሮ ካላቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናት።

Disclaimer: The official text of the website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram