በኢፌዲሪ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የተመራ እና የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይክተር ክቡር አቶ ጎሣ ደምሴ የሚገኙበት ልዑክ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ቆንሱል ጄኔራል ከክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ እና በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያውያን ኮሙዩኒቲ ማኅበር የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ጋር በጽ/ቤቱ ተገናኝተው ተወያዩ።
በውይይታቸው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ከመፈፀም አንፃር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተገበራቸው ያሉትን ዘርፈ-ብዙ የተቋሙ የሪፎርም ሥራዎች ማለትም የፓስፖርት ዕድሳትና ሥርጭት፣ የሊሴፓሴ፣ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ፣ የሰነድ አልባ ዜጎች ድጋፍ፣ በውጭ ሀገር የዜጎች ሥራ ሥምሪት፣ እንዲሁም በቪዛ አሰጣጥና ሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሥራ ግምገማ አካሄደዋል።
በማጠቃለያውም በቆንስላ ጄኔራል ጽቤቱና በኮሙዩኒቲ ማህበሩ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለው፣ በኦቶሜሽን የተደገፈ ለማድረግ የተጀመሩት ሥራዎችን በማጠናከር የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር በትኩረት መስራት እንደሚገባና ለዚህም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለሚሲዮኑ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ኃላፊዎቹ ገልፀዋል።

Disclaimer: The official text of the website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram