ክቡር አምሳደር ምስጋኑ አረጋ በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች ከሚገኙ የኮሚዩኒቲ አባላት ጋር ውይይት አካሄዱ፤
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች ከሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በዱባይ ውይይት አደረጉ። በውይይቱ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንሱል ጄኔራል ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደን ጨምሮ ዲፕሎማቶች፣ የኢትዮጵያዉያን ኮሚኒቲ ማህበር የአመራር ቦርድ አባላት የኮሙኒቲ ማህበር ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ተገኝተዋል።
 
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ለውይይቱ መነሻ ሃሳብ ባቀረቡበት ወቅት በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማኅበር በዱባይ እና ሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ የተቸገሩ ዜጎቻችንን በመርዳት፣ በሀገር ቤት ባለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገና በሌሎች ውጭ አገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያ፣ ትውልደ-ኢትዮጵያውያ እና የዳያስፖራ አደረጃጀቶች አርአያ የሆነ ማህበር መሆኑን ገልፀውዋል፡፡ በቀጣይም ይህንኑ አርአያነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ማህበሩ በችግር ውስጥ ላሉና ድጋፍ ለሚሹ የኮሚዩኒቱ አባላት ፈጥኖ-ደራሽ በመሆን ሁሉም ኢትዮጵያውያን በእኩልነት የሚያገለግል በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያውያን የአንድነትና ህብረት ማሳያ ሆኖ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን በለውጥ ጎዳና እየተጓዘች እንደመሆኗ መጠን፣ የለውጥ ሪፎርም ሥራዎች የዜጎች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር እያጋጠሙ ያሉትን ዓለምአቀፋዊ፣ አከባቢያዊና ሀገራዊ ውስብስብ ችግሮችን በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ሁሉም ዜጎች የጋራ ርብርብና ተሳትፎ እንደሚስፈልግ በአፅንኦጽት ገልፀዋል፡፡
 
በተያያዘም የጋራ ሀገራዊ ፈተናዎች በተለይም ድህነት፣ ኃላቀርነት፣ ዋልታ-ረገጥነት ለህብረ-ብሄራዊ አንድነታችን ፈተና ሆነው መቀጠላቸው እና ይህንኑ በውል በመገንዘብ ለሀገር በሚጠቅሙ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች ላይ በንቃት መሳተፍ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ አመላክተዋል፡፡ በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በተለይም የፓሰፖርት እድሳት መዘግየት፣ የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ ፈቃድ አሰጣጥ፣ የደንበኞች አገልግሎትን አሰጣጥ በተመለከተ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ወደ ሀገር ቤት ገብተው ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ የዳያስፖራ አባላት መንግስት ዕገዛ እንደሚያደርግ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡
AmharicArabicEnglish

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram