ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ አዲሷን የDP World የመካከለኛ ምስራቅና አፍሪካ ሀገራት የመንግስትና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር Mrs. Farida Mohammad ዛሬ ፌብሪዋሪ 02 ቀን 2023 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለዋል፡፡ ዳይሬክተሯ ከክቡር አምባሳደር ጋር ከተዋወቁ በኋላ ስለድርጅታቸው DP World ምስረታ፣ በአፍሪካ በተለይም በምስራቅ አፍሪካ ድርጅቱ እያካሄደ ያለውን የወደብና ሌሎች ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማትና አገልግሎቶች ኢንቨስትመንት አጠር ያለ ማብራሪያ አቅርበው፣ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ቢሮ መክፈቱንና የዋናው መስሪያ ቤታቸው ሰዎች ወደ አዲስ አበባና ጎሮቤት ሀገራት ለሚያደርጉ ተደጋጋሚ ጉዞ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው የትብብር ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡
 
ክቡር አምባሳደር አክሊሉ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ጋር ያላት የተሻለ የሁለትዮሽ ግንኙነት መነሻ መሰረት ሆኖ እሳቸውም ሆኑ ቆንስላ ጽ/ቤቱ ለሀገራዊ ጥቅም ከድርጅቱ ጋር ለመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑን፣ በተለይም ድርጅቱ በጎሮቤት ሀገራት የሚያደረገው የወደብና የተያያዥ ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት ግንባታና አገልግሎት ኢንቨስትመንት ትርፋማ መሆን የሚለችው ከሀገራችን ጋር በትብብር መስራት ሲቻል መሆኑን ሀገራችን በአካባቢው ትልቅ ገበያ መሆኗን በማሳየት ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ከዳይሬክተሯም ሆነ ከDP World ጋር በትብብር በሚሰሩ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ለመተባባርና አስፈላጊው ድጋፍ ለመስጠት ዝግጅ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
 
በውይይቱ ፍጻሜ ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ የDP World ዋና መስሪያ ቤት እና የዱባይ ትልቁን ወደብ (JAFZA) መሰረተ ልማትን እንዲጎበኙና ከድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንዲተዋወቁ የቀረበላቸውን ግብዣ ተቀብለዋል።
AmharicArabicEnglish

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram