የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2013 ወቅታዊ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ እንዲሁም ዜጋ ተኮር የዲፕሎማሲ እንቅስቀሴዎችን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህ መሰረትም፡-
  1. ከፖለቲካ ዲፕሎማሲ አኳያ፡-
    • የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ በቱርክ የስራ ጉብኝት በማድረግ ከቱርክ ጋር በውሃ ትብብር፣ በወታደራዊ ማዕቀፍ፣ በፋይናንስ ድጋፍ እና በወታደራዊ ፋይናንስ ዘርፎች የሁለትዮሽ ስምምነቶችን መፈራረማቸውን እንስተዋል።
    • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፋሪ ፊልትማን ጋር መወያየታቸውን አንስተው በውይይታቸውም ህወሃት ሰብአዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥፋቶችን እያደረሰ መሆኑ አቶ ደመቀ ጠቅሰው የአሜሪካ መንግስት ቡድኑን አለማውገዝ የሁለቱ አገሮች የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ያላገናዘበ መሆኑን አንዳነሱላቸው ጠቅሰዋል። በወቅቱም አምባሳደር ጄፋሪ ፊልትማን የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ በህወሃት ላይ ያለውን አመለካከት በውል እንደሚረዱ ገልጸው፤አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ሠላም እና አንድነት በማስጠበቁ፣ በማረጋገጡ እና በማስቀጠሉ ላይ የተመረኮዘ ፖሊሲ የሚትከተል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በሁለቱ አገራት መካከለ ያለው ግንኙነት ቀጠናዊ ትርጉም ያለው መሆኑን መግለጻቸን አንስተዋል።
    • በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጭ ጉዳይና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለነበሩ የምክር ቤት አባላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእውቅና መርሃ-ግብር ማከናወኑን አንስተዋል። በወቅቱም የቋሚ ኮሚቴው አባላት ለነበሩ 29 የምክር ቤት አባላትና አስተዳደር ሰራተኞች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የእውቅና የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል። ክብርት ሚኒስትር ዴአታዋ የምክር ቤቱ አባላት በነበራቸው የስራ ዘመን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ላደረጉት ተሳትፎ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል።
በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ መ/ቤታችን ሁለት የፕሬስ መግላጫዎችን ማውጣቱን በተመለከተ፣
  • አምኒስቲ ኢንተርናሽናል በትግራይ ክልል አስገድዶ መድፈር እና ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሟል በማለት ባወጣው ሪፖርት በርቀት በተደረገ ቃለ መጠየቅ መሆኑና በበሱዳን የሳምሪ የሚባሉ ቡድኖች ዋቢ አድርጎ ታዓማንነት የጎደለው መሆኑን ተጠቅሷል፡፡ በገለልተኛ አካላት ተጨማሪ ማጣሪያ ይደረግ ዘንድ የተመድ ሰብአዊ ቢሮ እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን ማጣሪያ እያደረጉ መሆኑን ያልተገናዘበ የፖለቲካ እና የጥራት ችግር ያለው ሪፖርት እንደሆነ በመግለጫው መጠቀሱን አንስተዋል።
  • አሸባሪው ህወሓት ቡድን በአፋርና የአማራ ብሔራዊ ክልሎቸ የተለያዩ አካባቢዎች በከፈተው ጥቃት የኢትዮጵያ ህዝብ የባህል፣ የእምነት እና የማንነት መገለጫ በሆኑ እድሜ ጠገብ ቅርሶች ላይ የደህንነት ስጋት መደቀኑን በማውሳት በአገሪቱ የሚገኙ ቅዱሳ ቦታዎች እና ተቋማትን ደህንነት ለመጠበቅ መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም የአሸባሪውን ቡድን የጥፋት ድርጊት እንዲያወግዝ መንግስት ጥሪ ያቀረበበትን መግለጫ ማውጣቱን አስታውሰዋል።
  • በሌላ መግለጫ የህወሓት ቡድን እየወሰደው ያለውን ወቅታዊ የሽብር ተግባር የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም እንደመልካም አጋጣሚ በመ ጠቀም በአፋር እና አማራ ብሔራዊ ክልሎች በሚገኙ ወረዳዎች ወረራ በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ እና ከ300 ሺህ በላይ እንዳፈናቀለ፣ መንግስተ ለትግራይ እርዳታ ፈላጊዎች በተፋጠነ ሁኔታ እንዲደር የተቻለውን እንደሚያደርግ እንዲሁም እርዳታው በአማራ እና አፋር የሚገኙ ተፈናቃዮችንም ማካተት እንዳለበት፣ መከላከያ የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ስምሪት የሰጡ የሽብር ቡድኑ መሪዎች ተገቢው ፍርድ እንዲያገኙ መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ፣ከህግ መንግስታዊ ስርዓቱና ህዝብ በድምጹ ካረጋገጠው ፍላጎት በተቃረነ ሁኔታ የሚደርሱ የውጭ ተጽዕኖዎችን የማይቀበል መሆኑን መገለጹን አንስተዋል።
በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደሮች ተቀማጭ በሆኑባቸው አገራት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ የማስጨበጥ እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ተግባራት ማከናወናቸውን በተመለከተ፡-
  • በደቡብ ሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር እና የመንገዶችና ድልድዮች ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን፣
  • በሴኔጋል የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ከሴኔጋል የንግድ ሚስትር ክብርት አሚናታ አሶሜ ዲያታ ጋር በሁለቱ አገራት መከላከል ያለውን ኢኮኖሚ ግንኙነት በተመለከተ ዉይይት ማካሄዳቸው፣
  • በባህሬን ቆንስል ጽ/ቤት ጄነራል ከባህሬን የኢንዱስትሪ፤ ንግድና ቱሪዝም ሚንስትር ጋር በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማካሄዳቸው፣
  • በሳዑዲ አረቢያ የኢፌዲሪ አምባሳደር ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ደኤታ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በሳኡዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደረገው አፈሳ እንዲቆም እንዲሁም በሳኡዲ አረቢያ የምህረት አዋጅ ተግባራዊ በሚሆንበት ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
2. ከኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አኳያ፡-
  • ዶሃ፣ ቤጂንግ እና ዋሽንግተን በሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲዎች አስተባባሪነት የሀገራችንን የኢንቨስትምንት ዕድሎች ለየአገሮቹ ባለሀብቶች በበይነመረብ የማስተዋወቅ ሥራ መከናወኑ፣
  • አልጀሪያ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አስተባባሪነት የኢትዮጵያ እና የአልጄሪያ የቢዝነስ ካውንስል መመስረቱ፣
  • ቴል አቪቭ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ የተመለመለ 10G Green Gigawatt የተባለ የእስራኤል ኩባንያ የታዳጊ ሀገራት የልማት ፍላጎት መሠረት ያደረገ የኃይል አቅርቦት ላይ የተሰማራ ሲሆን በሀገራችንም በዘርፉ ለመሰማራት የኩባንያውን ተወካዮች ወደ ሀገራችን በመላክ የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት ማድረጉ፣
  • ጓንጆ እና ቴል አቪቭ በሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲኖች አስተባበሪነት የአገራችንን የኢንቨስትመንት ዕደሎችን በተመለከተ በየአገሮቹ ፍላጎት ላላቸው ባለሀብቶች በበይነ-መረብ ገልጻ መደረጉ፣
  • የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ከህንድ የቢዝነስ ፎረም አባላት ጋር ውይይት ያካሄዱ ሲሆን፣ ህንድ በኢትዮጵያ የምታደርገውን የቀጥታ ኢንቨስትመንት ተሳትፎ ማሳደግ ስለሚቻልበት መንገድ መምከራቸው፣
  • እ.ኤ.አ. ከኦክቶበር 01 ቀን 2021 እስከ ኤፕሪል 31 ቀን 2022 በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ዱባይ በሚካሄደው ዓለም ዓቀፍ ኤክስፖ ላይ ተሳትፎ ለማድረግ የንግድ ፣ባህል ፣የቱሪዝም መስህቦች እና ታሪክ ይዘት ፕሮግራሞች ላመቅረብ ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑ፣
  • እ.ኤ.አ. ከሴምቴምበር 26-28/2021 ድረስ በሚካሄደው 2ኛው የቻይና-አፍሪካ ኢኮኖሚና ንግድ ኤክስፖ በቻይና አገር በቻንግሻ ከተማ በሚካሄደው ላይ ሀገራችን የክብር እንግዳ ሆና በኤክስፖው ላይ እንድትሳተፍ በመጋበዟ በንግደና ኢንዳስትር ሚ/ር አስተባባሪት የቅደሚያ ዝግጀት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ፣
  • እ.ኤ.አ. ከኦክቶበር 22-23 ቀን 2021 ድረስ በአሜሪካ አገር ሊካሄዱ የታቀዱ የንግደ ትርኢቶችን በኒው ኦርሊየንስ ለማካሄድ በታቀደው የባለ ልዩ ጣዕም የቡና ኤክስፖ መ/ቤታችን ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንና ከሌሎች ጋር እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት አሜሪካ ከሚገኘው Ethio-Promotion LLC ጋር በመተባበር በዋሽንግተን ዲሲ እየተዘጋጀ ላለው ኢትዮ-ዩ.ኤስ. የንግድ ትርኢት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ፣
  • በቴል አቪብ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢምባሲ ከእስራኤል የላኪዎች እና ዓለም አቀፍ ንግድ ትብብር ተቋም (Israeli Export and International Cooperation Institution) ጋር በመተባበር በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ በተቋሙ አዳራሽ የክብ ጠርጴዛ (Round Table) ምክክር መደረጉ፣
  • በቴል አቪብ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢምባሲ ከእስራኤል የላኪዎች እና ዓለም አቀፍ ንግድ ትብብር ተቋም (Israeli Export and International Cooperation Institution) ጋር በመተባበር በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ በተቋሙ አዳራሽ የክብ ጠርጴዛ (Round Table) ምክክር አድርጓል።
3. ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አኳያ፡-
  • ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከጂቡቲ 49፣ ከኬንያ 43፣ ከሱዳን 60 ዜጎች እንዲሁም ከየመን-ሰነዓ 79 ዜጎች በድምሩ 231 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሷል።
  • ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሰኝ ኩነት ኤጀንሲ እና ከIOM የተዉጣጣ ኮሚቴ ከነሓሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደ የመን ኤደን ተጉዟል፡፡ ቡድኑ ወደ 4000 ለሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ኢትዮጵያዉ ዜግነታቸዉን አጣርቶ የጉዞ ሰነድ መስጠት ጀምሯል፡፡
  • በሳኡዲ አረቢያ በተለያዩ ማቆያ ማዕከላትና እስር ቤቶች የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያንን በተመለከተ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በሳምንት ሶስት በረራዎችንና ከ1000 ዜጎችን ለማምጣት የቅድመ ዝግጅት ሥራ የተከናወነ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር ዜጎች መግባታቸወን፣ ይህ ሂደት ህፃናት የያዙ እናቶችን፣ የጤና ችግር ያለባቸውን እና ባለፈው ጊዜ ለመመለስ በሂደት ላይ ቆይተው በተለያየ ምክንያት ያልተመለሱትንና በተደጋጋሚ ጊዜ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያልሄዱትን ቅድሚያ በመስጠት የሚከናወን መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለያዩ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ፣ ለአገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ድጋፍ በተለያየ መንገድ ገቢ በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ።ከእነዚህ መካከል፡-
ለአብነትም፡-
  • የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ጥምረት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ ዳያስፖራው ከመንግሥት ጎን በመሆን ለአገሩ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡን፣
  • የኢትዮጵያ ዳያስፖራው የሠላም ጓድ፣ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ማህበር እንዲሁም የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመመከት እንደሚሰራ አቋማቸውን መግለጻቸውና የቡድኑ አባላት በአገራችን በነበራቸው ቆይታ ከተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን፣
  • በቤልጂየም፣ ሉግዘምበርግ እንዲሁም በጣሊያን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን የተቀናጀ ዘርፈ ብዙ ጫና ለማውገዝ እና የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለውን የአገር ህልውና የማስቀጠል ትግል ለመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው፣
  • በኒውዮርክ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከ62 ሺህ ዶላር በላይ፣
  • በፍሎሪዳ ጃክሰንቪል እና አካባቢዉ የምትገኙ ወገኖቼ በኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖቻችን $67,908 የአሜሪካን ዶላር፣
  • በዳላስ አብሮነት ምሽት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በአንድ መድረክ ከ$140,000 የአሜሪካን ዶላር በላይ፣
  • ኖርዌይ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብና የሲቪክ ማኅበራት ለተፈናቀሉ ወገኖች የ1,360,000 ብር ድጋፍ
  • በደቡብ ሱዳን በጁባና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልዳ-ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከኤምባሲው ዲፕሎማቶች 965,143 (ዘጠኝ መቶ ስልሳ አምስት ሺህ አንድ መቶ አርባ ሦስት ብር በላይ) ድጋፍ፣
  • በአውስትራሊያ 25 ሺህ ዶላር የመከላከያ ኃይላችንን ለመደገፍ ቃል የተገባ፣
  • በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማት በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞንና ሰሜን ሸዋ ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች $16,415 የአሜሪካን ዶላር፣
  • አቡዳቢ የሚገኘው የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ማኅበር ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የ14 ሚሊየን ብር ድጋፍ፣
  • በሱዳን ለአገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ማሰባሰቢያ እና ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ፕሮግራም ተካሄደ፣ ለመከላከያ ሰራዊት ማጠናከሪያ 5,725 የአሜሪካ ዶላር ተለግሷል፡፡ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ደግሞ የ6,100 የአሜሪካ ዶላር የቦንድ የተሸጠ ሲሆን 7,600 የአሜሪካ ዶላር ቃል የተገባ በርካታ ድጋፍ መደረጉን
  • በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፣ በአቡዳቢና ዱባይ ሚሲዮኖች ዲፕሎማቶች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍ የሚውል የ14 ሚሊየን ብር መሰባሰቡን፣
  • በጀርመን-በርሊን የኢትዮጵያ ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አስተባባሪነት “አንድነት ለሀገር ህልውና እና ሉዓላዊነት!” በሚል መርህ ቃል በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ እና ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ‘It Is My Dam’ የተባለ ዲጂታል መተግበሪያ (GERD fund raising digital Application) ማስተዋወቂያ እና የዌብነር ውይይት ማካሄዱንና በዝግጅቱ በጀርመንና የኢትዮጵያ ኢምባሲ በርሊን የሚሽፍናቸው አገሮች፣ የአውሮፖ ክላሥተር የዳያስፖራ መሪዎችና አባላት በቋሚነት በየወሩ ለሀገር ህልውና ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ለግድቡም ድጋፍ መተግበሪያውን በመጠቀም መደገፍ መቀጠላቸውን አንስተዋል።

Disclaimer: The official text of the website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram