የኤች ኤንድ ኤም ግሎባል ቬንቸርስ (H&M Global Ventures) ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ባቀረቡት የኢንቨስትመንት ፕሮፖዛል ላይ ጥልቅ ውይይት ተደረገ፤ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ ከኤች ኤንድ ኤም ግሎባል ቬንቸርስ (H&M Global Ventures) ዋና ሥራ አስፈጻሚ Mr. David R. S Muller እና ከአጋራቸው Dr. Biruktawit Mafito ጋር በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ባቀረቡት የኢንቨስትመንት ፕሮፖዛል ላይ ጥልቅ ውይይት አደረጉ።በቀረበው ፕሮፖዛል ላይ በተደረገው ገለጻ መሰረት ከገለጻው ለመረዳት እንደተቻለው ኩባንያው በጤና፣ በግብርና፣ በትምህርት እና በመከላከያ ኢንዱስትሪዎች ላይ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በኢትዮጵያ ለመሰማራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አሳይቷል። ዋና ስራ አስፈፃሚው እንደገለጹት ኢትዮጵያን በቅርበት እንደሚያውቋት፣ ጥልቅ ጥናቶችን እንዳደረጉ እና ኢንቨስትመንት ለማድረግም መንገዶች የተሳኩና ቀላል ሊያደርጉ የሚችሉ ኔትወርኮችን እንደዘረጉ የሚያሳይ ነው። በዚህም ረገድ አምባሳደር አክሊሉ እንደገለጹትም በቆንስላ ጽ/ቤት በኩል ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም አረጋግጠውላቸዋል።