ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዛሬው ዕለት ህዳር 2 ቀን 2015 ዓ.ም በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የተለያዩ የሥራ ክፍሎችን ጉበኙ።
በጉብኝቱ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት፣ የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር፤ የዳያስፖራ ተሳትፎን ለማሳደግ እንዲሁም በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በቱሪዝም መስኮች አገራችንን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተደረገ ስላላው የሥራ እንቅስቃሴ ገለጻና ማብራሪያ በክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ ተደርጎላቸዋል።
ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች ከኢትዮጵያዊን ኮሚኒቲ ማህበር እንዲሁም አቡዳቢ ከሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ እና ኮሚኒቲ ማህበር፣ ከአገሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተሳሰር እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።
ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱና ኮሚኒቲ ማህበሩ በጋራ በመቀናጀት የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ እያደረጉት ያለው ሥራ አበረታች መሆኑን ገልጸው፣ መንግስት ባለው ውስን ሀብት ብቻ የዜጎችን ችግሮች መፍታት የማይችል በመሆኑ ሁሉም የዳያስፖራ አባላትና አደረጃጀቶች የዜጎችን መብትና ጥቅም በማስጠበቅ ዙሪያ የቆስላ ጽ/ቤቱ እና የኮሚኒቲ ማህበሩ በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በጉብኝቱ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ክቡር አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬትቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር፣ ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ቆንስል ጄኔራል፣ የሚሲዮኑ ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች ፣ የኮሚኒቲ ማህበሩ ቦርድ አመራር አባላትና ጽ/ቤት ሠራተኞች ተገኝተዋል።
በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት እ.ኤ.አ በ2004 የተከፈተ ሲሆን፣ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከማጠናከር ጎንለጎን በተለይ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ የዜጎችን መብትና ጥቅም የማስጠበቅ፣ የዳያስፖራን ተሳትፎ የማሳደግ እና የሀገራችንን የንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ማስፋፋት እንዲሁም የገጽታ ግንባታና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እየሠራ ይገኛል።
AmharicArabicEnglish

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram